Mortena Jeru Werda Communication

Mortena Jeru Werda Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mortena Jeru Werda Communication, Government Organization, Moretena Jeru, north Shewa, Martinez, CA.

A leading role in the Queen's Communication Information Sector: Integrating our vision for the success of our mission by raising public awareness of basic police strategies and programs by raising public awareness of basic police strategies and programs

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ላሻው በመስጠት ሀገር ወዳድነቱን እና የዴሞክራሲ ልምምድ ፍላጎቱን  በተግባር አሳይቷል። ድምጽ የመስጠቱ ሂደት ማለዳ 12:00 ጀምሮ ሲካሄድ...
06/02/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ላሻው በመስጠት ሀገር ወዳድነቱን እና የዴሞክራሲ ልምምድ ፍላጎቱን በተግባር አሳይቷል።

ድምጽ የመስጠቱ ሂደት ማለዳ 12:00 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ቢሆንም ምሽት 12:00 ድረስ ባለመጠናቀቁ ምርጫ ቦርድ መራጩ የመምረጥ መብቱን እንዲጠቀም እስከ ለሊት 6:00 አራዝሞለት መራጩም እድሉን ተጠቅሟል።

በዚህ ምርጫ ህዝቡ እኔ አውቅልሃለሁ ለሚለው ሁሉ፣ በሰላም ወጥቶ በመምረጥ ባሳየው ቁርጠኝነት አይ እኔ ለራሴ አውቃለሁ፣ ሀገሬን በሰላማዊ መንገድ ለትውልድ አሻግራለሁ ያለበት ነው።

ድምፁን ይወክለኛል ላለው በነፃነት ያለማንም ጫና ሰጥቷል።

በዚህ ምርጫ የተሳተፈው የመራጭ ቁጥር እና የመራጩ ጨዋነት ሲታይ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንጂ ጩኸትና የጠብመንጃ ማስፈራሪያ አያስፈልገኝም ያለበት ነው።

እናም ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር ጠብመንጃ እያወዛወዙ በኃይል ካልገዛሁህ ለሚሉት ሁሉ መሻታቸው ጊዜ ያለፈበት ተረት ተረት መሆኑን በተጨባጭ በድምጹ ወስኗል።

የሚበጀውም የህዝቡን የካርድ ምርጫ መጠበቅና ውሳኔውን መቀበል ብቻ ነው።

ህዝቡ አንዴ ወስኗል። ኢትዮጵያ የፍላጎቷን መርጣለች፤ ለውጤቱ ደግሞ ምርጫ ቦርድን ብቻ በትእግስት መጠበቅ ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያንን በቅጡ የማያውቁ አካላት ሊለዩን፣ ሊበትኑን ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ከባእዳን በተጨማሪም የውስጥ ባንዳዎች ብዙ ጥረዋል።

ነገር ግን ለልዩነት የማንመች እና እርስ በራስ የተሰናሰልን ሀገራችንን የምንወድ ህዝቦች በመሆናችን ዛሬ ደርሰናል።

ትናንት ለሚወክለን ካርዳችንን በነጻነት ሰጥተናል።

በዚህ ዙርም ሊያውኩን ሞከረዋል፤ ነገር ግን አልሆነላቸውም፤ እኛ የዴሞክራሲ ልምምድን መርጠናል።

እነሱ ገና የድንጋይ ዘመን ላይ ናቸው። ወጋችንም አይገጥምም።

እኛ የጀግኖቹ የእናት አባቶቻችን ልጆች ነን።

ቀደምት እናት አባቶቻችን ከግል ፍላጎታቸው ይልቅ ለሀገራቸው ቅድሚያ በመስጠት የላብ፣ የደም፣ የአጥንት እና የህይወት መስዋእትነት ከፍለው ሀገር አውርሰውናል።

የአሁኑ ትውልድም ሀገሩን በሰላምና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለቀጣይ ትውልድ ለማሻገር በካርዱ ወስኗል።

በካርዳችን የሚሻንን መርጠናል። ማንም ቢያሸንፍ ሀገር ከፖለቲካ እና ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ ናት።

አብሮነታችን ውበታችን ነው። በእናት አባቶቻችን ሀገር ወዳድነት ኢትዮጵያን ወርሰናል። እኛም በድምጻችን ሀገር ለማሻገር ተልመናል። ጉዟችን ወደ ሰላማዊው ዴሞክራሲ ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ መርጣለች! ውሳኔዋንም እንቀበላለን!

🇪🇹🗳️ ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!የሞረትና ጅሩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት  አቶ ወርቃለማሁ ሀይሌእና የሞረትና ጅሩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት  ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ ...
06/01/2026

🇪🇹🗳️ ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!
የሞረትና ጅሩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አቶ ወርቃለማሁ ሀይሌእና የሞረትና ጅሩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ ምኒችል ምርጫጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጡ።
**************
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም፡ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አቶ ወርቃለማሁ ሀይሌእና የሞረትና ጅሩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ ምኒችል ምርጫጣቢያ ተገኝተው የ7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ድምጽ ሰጡ።

 #ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!!በሰሜን ሸዋ  ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ  እና የእነዋሪ የምርጫ ክልል የክልል ም/ቤት የብልጽግና እጩ ተወካይ ክቡር አቶ ብዙሀን አሰፋ  ድምጽ ...
06/01/2026

#ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!!
በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የእነዋሪ የምርጫ ክልል የክልል ም/ቤት የብልጽግና እጩ ተወካይ ክቡር አቶ ብዙሀን አሰፋ ድምጽ ሰጡ።

ግንቦት 24/2018ዓ/ም የ( ሞ.ጅ.ወ.መ.ኮ)
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የእነዋሪ የምርጫ ክልል የክልል ም/ቤት እጩ ተወካይ ክቡር አቶ ብዙሀን አሰፋ በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሞረትና ጅሩ ወረዳ ድምፅ ሰጥተዋል።

 #ኢትዮጵያ ትመርጣለች !ግንቦት 24/2018ዓ/ም የ( ሞ.ጅ.ወ.መ.ኮ)በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ  የ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ የምርጫ ጣቢያዎች  በሰላማዊ ...
06/01/2026

#ኢትዮጵያ ትመርጣለች !
ግንቦት 24/2018ዓ/ም የ( ሞ.ጅ.ወ.መ.ኮ)
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ የ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ የምርጫ ጣቢያዎች በሰላማዊ መንገድ ይበጀኛል የሚለውን መንግስት ለመምረጥ ምርጫው እንደቀጠለ ነው ።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!‎‎በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ አስተዳደር የጅሁር ከተማ   ህዝቡ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት  ይበጀኛል የሚለውን መንግስት ለመምረጥ  በማለዳ ተሰልፎ በሰላማዊ መ...
06/01/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

‎በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ አስተዳደር የጅሁር ከተማ ህዝቡ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ይበጀኛል የሚለውን መንግስት ለመምረጥ በማለዳ ተሰልፎ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን እየሰጠ ነው።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነዉ!‎በሞረትና ጅሩ አስተዳደር በሁሉም ቀበሌዎች ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠት ጀምረዋል።
06/01/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነዉ!
‎በሞረትና ጅሩ አስተዳደር በሁሉም ቀበሌዎች ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መራጮች ድምጻቸውን መስጠት ጀምረዋል።

05/29/2026
05/27/2026
05/27/2026
05/27/2026

Address

Moretena Jeru, North Shewa
Martinez, CA
251116880051

Telephone

+251116880051

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mortena Jeru Werda Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share