Financial Intelligence Service-Ethiopia

Directions Website Contact the organization

Financial Intelligence Service-Ethiopia ይህ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ ነው።This is official page of Financial Intelligence Service of Ethiopia.

23/10/2026

የሪል ስቴት ዘርፍ ML-TF አደጋ ጥናት ውጤትና መፍትሔዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

21/10/2026

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና የተለያየ ግለሰቦች ላይ የከባድ ሙስና እና በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል ክስ ቀረበ።
*************
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ በነበረው አቶ ብርሀኑ አለቃ አስገዶም ላይ በተደራራቢ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበታል። የተሰጠውን ሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል 1,134,609,241.93 (አንድ ቢሊየን አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሚሊየን ስድስት መቶ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ አርባ አንድ ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ያገኘ መሆኑም ተጠቅሷል።

በተመሳሳይም ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች፣ የሠራተኛና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ሌሎች ግለሰቦች ጨምሮ 13 ሰዎች ላይ ክስ ቀርቧል፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ ከባድ ሙስና ወንጀል ችሎት በተመሰረተው ክስ ብርሀኑ አለቃ አስግዶም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (Ethiopian Labour Market Information System) ላይ ወደውጭ ሀገራት ለሥራ የሚጓዙ እና የሙያ ብቃት ምዘና ሊጸድቅላቸው (COC Online) የሚገቡ ዜጎችን ያለ ምንም ወይም ያለ በቂ ሥልጠና የተለያየ መጠን ያላቸውን ገንዘቦችን በማስከፈል የሙያ ብቃት ምዘና እንዲጸድቅላቸው በማድረግ፤ ከፍተኛ የሆነ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለማይታወቁ (የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኛ ላልሆኑ) ግለሰቦች በሲስተሙ ላይ የሙያ ምዘና (COC) የማጽደቅና የሙያ ምዘና ልዩ የአስተዳዳሪ (COC Special Admin) ሥልጣን እንዲኖራቸው በማድረግ፤ ከዚህ ወንጀል ድርጊት ወደ ውጭ ሀገራት ከሚሄዱ ዜጎች የሚሰበሰቡ ገንዘቦችን ለመቀበል ዓላማ በሀሰተኛ መታወቂያ ስማቸዉን እንዲቀይሩ በማስደረግ እና የሌሎች ሰዎችን ፎቶ በመጠቀም በተለያዩ ባንኮች የባንክ ሂሳብ በማስከፈት 1,134,609,241.93 (አንድ ቢሊየን አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሚሊየን ስድስት መቶ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ አርባ አንድ ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) መጠን ያለው ገንዘብ በእነዚህ የሂሳብ ቁጥሮች እንዲገባ በማድረግ፣ ከእነዚህ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ክፍያ በመፈፀም በራሱና እና ተከሳሽ በሆነችው ባለቤቱ ስም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6 መኖሪያ ቤቶች በ223,654,950 (ሁለት መቶ ሀያ ሶስት ሚሊየን ስድስተ መቶ ሀምሳ አራት ሺህ ዘጠን መቶ ሀምሳ) ብር፤ በ68,144,738.03 (ስልሳ ስምንት ሚሊየን አንድ መቶ አርባ አራት ብር ከሶስት ሳንቲም) ብር አንድ ዘመናዊ ተሽከርካሪ የገዛ በመሆኑ፣ ተከሳሽ ብርሃኑ አለቃ በዋና ወንጀል አድራጊነት ለጊዜው ካልተያዘው ተከሳሽ ታምርአየሁ ጌትነት ጋር በመሆን በፈጸሙት ሥልጣን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ብርሃኑ አለቃ ላይ በወንጀል የተገኘን ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል፣ ከባድ እምነት ማጉደል፣ ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት ወንጀልን ጨምሮ በአጠቃላይ 4 ተደራራቢ ክስ ቀርቦበታል፡፡

በሌላ በኩል ተከሳሽ ኤርሚያስ ተክሉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሰራተኛ ስምሪት መሪ ሥራ አስፈጻሚ በነበረት ወቅት ወደ ጆርዳን ሀገር 64,091 (ስልሳ አራት ሺህ ዘጠና አንድ) ዜጎችን በሀሰተኛ የቪዛ ሰነዶች ከሀገር እንዲወጡ በማስደረጉ ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

በአጠቃላይ በዚህ የምርመራ መዝገብ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሠራተኞችን ጨምሮ፣ የብርሃኑ አለቃ ባለቤት፣ የሥራና ሠራተኛ ኤጀንሲ ባለቤቶችን እና ሌሎች ግለሰቦችን ጨምሮ በ13 ሰዎች ላይ እንደየተሳትፏቸው በጉቦ መቀበል፣ በሥልጣን መነገድ እና በወንጀል ድርጊት የተገኘውን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀሎች 16 ክሶች ቀርቦባቸዋል።
የቀረበውን ክስ ለመስማት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ለጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

የችሎት ሒደቱን በቀጣይ እየተከታተልን ወቅታዊ መረጃዎችን የምናደርስ መሆኑን እየገለጽን በሙስና ወንጀል ላይ የተጀመረውን የሕግ ማስከበር ሥራ ከምንጊዜውም በላይ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።

የሪል ስቴት ዘርፍ ለሀገር ግንባታ ያለውን ሚና ማበረታትና የወንጀል መጠቀሚያ እንዳይሆኑ መጠበቅ ይገባል---------------------------------------አዲስ አበባ (ጥቅምት 11...
21/10/2026

የሪል ስቴት ዘርፍ ለሀገር ግንባታ ያለውን ሚና ማበረታትና የወንጀል መጠቀሚያ እንዳይሆኑ መጠበቅ ይገባል
---------------------------------------
አዲስ አበባ (ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም) ፦ የሪል ስቴት ዘርፍ በሀገር ዕድገትና ኢኮኖሚ ልማት ውስጥ የሚጫወታው አዎንታዊ ሚና እንዳለ ሆኖ በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ለማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ ለመደገፍ ወንጀል እንዳይውል ተገቢውን ቁጥጥርና ጥበቃ ሊደረግበት እንደሚገባ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው «የሪል ስቴት ዘርፍ በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ መጠቀም እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት አደጋ (ስጋት-ተጋላጭነት) ጥናት»ን አስመልክቶ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚመለከታቸው አካላት በተሳተፉበት በመካሄድ ላይ ባለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ መድረክ ላይ ነው።

በተባበሩት መንግስታት የፀረ-አደንዛዥ ዕፅ ቁጥጥር ቢሮ (UNODC) የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ አብርሃም ልየው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት የሪል ስቴት ዘርፍ ለሀገር ዕድገትና ኢኮኖሚ ከፍተኛ አዎንታዊ ሚና ያለው ቢሆንም ወንጀለኞች በሕገ-ወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስለው ለመጠቀም በይበልጥ ትኩረት የሚያደርጉበት ዘርፍ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።

አቶ አብርሃም አክለውም ዘርፉ ካለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንፃር መደገፍና ማበረታት እንዳለበት። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ የወንጀለኞች መጠቀሚያ እንዳይሆን ወንጀሉን አስቀድሞ መግታት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው የሪል ስቴት ዘርፉን ከሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመደገፍ የመጠበቅ ሃላፊነት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የግሉ ዘርፍም የጋራ ሃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል።

በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የሱፐርቪዥንና ኮምፕሊያንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ተመስገን በበኩላቸው የሪል ስቴት ዘርፉ ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚደረግበት በመሆኑ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ጠቅሰዋል። አቶ ሙሉጌታ እንደገለጹት በጥናቱ የቀረበው የሪል ስቴት ዘርፍ የስጋት ተጋላጭነት ዳሰሳ (Real Estate Money Laundering and Financing of Terrorism Sectoral Risk Assessment) ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ ያለው ሲሆን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ከዚህ ቀደም የነበሩ ክፍተቶችን ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል። በጥናቱ ዝግጅት ላይ ለተሳተፉ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሽብርተኝነት ፋይናንስ ስጋት-ተጋላጭነት ጥናት መሰረት የቀረቡ ምክረ-ሀሳቦች------------------------------------------------------...
20/10/2026

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሽብርተኝነት ፋይናንስ ስጋት-ተጋላጭነት ጥናት መሰረት የቀረቡ ምክረ-ሀሳቦች
--------------------------------------------------------
ሽብርተኝነትን በገንዘብ ፋይናንስ ማድረግን በተመለከተ ለትርፍ ያልተቋቋሙ (የሲቪል ማህበረሰብ) ድርጅቶች አደጋ ዳሰሳ ጥናት (NPOs Terrorism Financing and Risk Assessment) ግኝቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሁለት ቀናት ወርክሾፕ ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ተጠናቋል።

በወርክሾፑ ላይ በተደረገው ውይይት እንደተመላከተው በጥናቱ ለወንጀሉ ያላቸው አደጋ በከፍተኛ ስጋትነት የተለዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወንጀለኛ ናቸው ማለት ሳይሆን በጥናቱ በተለዩ ምክንያቶች ጠንከር ያለ የመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው አመላካች መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የዓለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ተሞክሮ እንደሚያሳየው ለትርፍ ያልተቋቋሙ (የሲቪል ማህበረሰብ) ድርጅቶች ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል መጠቀሚያ የሚሆኑበት ዕድል መኖሩን ተመላክቷል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ የ2026 የሲቪል ማህበረሰብ (ለትርፍ ያልተቋቋሙ) ድርጅቶች ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት አደጋ ግምገማ ሪፖርት (NPO Terrorism Financing Risk Assessment Report) መሰረት ወንጀሉን ለመግታት ከቀረቡት ዋና ዋና ምክረ-ሀሳቦች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። እነሱም፦

1. የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን ማጠናከር፦ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት እና እና የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በከፍተኛ የሽብርተኝነት የገንዘብ ድጋፍ አደጋ ውስጥ ሊወድቁ የሚችሉ ድርጅቶችን በመለየት፣ ስለአደጋዎቹ እና ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የመከላከያ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማጎልበቻ እና የስልጠና መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀት እና ማጠናከር እንደሚጠበቅ፣

2. በተቋማት መካከል ያለን ትብብር ማጠናከር፦ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍን ለመከላከል የሚደረግ መረጃ ልውውጥ፣ የምርመራ፣ የክስ እና በህገ-ወጥ ተግባር ውስጥ የተሳተፉ አካላትን ንብረት መውረስን ጨምሮ የፌዴራል ተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅትና ትብብር ማጠናከር በዳሰሳ ጥናቱ የቀረበው ሌላው ምክረ-ሀሳብ ነው።

3. ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና መልካም አስተዳደርን ለማሻሻል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቶችን እንዲዘረጉ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

4. የክልል ባለሥልጣናትን አቅም መገንባት፦ የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በየክልሉ የሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቃሴዎችን በበቂ ደረጃ ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ድጋፍ ማድረግ እና አቅማቸውን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ምክረ-ሀሳብ ቀርቧል።

5. የፋይናንስ ግብይቶች ክትትልን ማሻሻል፦ በባንኮች እና በሞባይል ገንዘብ አገልግሎት አቅራቢዎች የሚደረጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የገንዘብ ዝውውሮች ላይ ክትትል የማጠናከር እንዲሁም ማንኛውም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ወዲያውኑ ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ሪፖርት መደረጉን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።

6. ሕጋዊ የባንክ ሥርዓቶችን መጠቀምን ማበረታታት፦ ህጋዊ የባንክ ቻናሎችን በመጠቀም በሃዋላ እና በጥሬ ገንዘብ የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮችን መቀነስ ላይ አተኩሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑ፤

7. የደንበኛ ማንነት መለያ መመሪያዎችን ማሻሻል፦ በለጋሾች በኩል የሚደረጉ የገንዘብ ግብይቶችን እና ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ዝውውሮችን መሠረት ያደረጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ደንበኞችን የሚመለከት የተሻሻለ የደንበኛ መለያ መመሪያዎችን ማዘጋጀትና መተግበር እንደሚያስፈልግ።

8. በሲቪል ማህበረሰብ የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች ላይ የጥንቃቄ እርምጃ መውሰድ፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞችን የሚጠቀሙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሠራተኞቻቸውን ማንነት በሚገባ የማጣራት እና የቅጥር ሂደታቸውን የማጠናከር እንዳለባቸው ምክረ-ሀሳብ ቀርቧል።
-----------------//------------

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሽብርተኝነት በገንዘብ መደገፍ መጠቀሚያ ላለመሆን-------------------በሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን በመከላከል አውድ ውስጥ ለትርፍ ያልተቋ...
20/10/2026

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሽብርተኝነት በገንዘብ መደገፍ መጠቀሚያ ላለመሆን
-------------------
በሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን በመከላከል አውድ ውስጥ ለትርፍ ያልተቋቋሙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለይም ከፍተኛ ስጋት ባላቸው አከባቢዎች እና ግጭት አከባቢ የሚሰሩት ስጋት-ተጋላጭነትን መሰረት ያደረገ የመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ አንፃር መደረግ ካለባቸው
1. የአደጋ ግምገማ ማካሄድ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቱን የስራ ባህሪ፣ ዒላማ የተደረጉ ማህበረሰቦችን እና ገንዘብ የሚሰበሰብባቸውን ወይም ወጪ የሚደረግባቸውን ጂኦግራፊያዊ አከባቢያዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ በጉድለት እና በስጋት መልክ ጉዳዮችን ለይቶ ማወቅ እና መገምገም ይጠበቃል፣

2. የፋይናንስ ግልጽነትን መጠበቅ፦የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚፈፅሟቸው ክፍያዎች እና የገንዘብ ዝውውሮችን በጥሬ ገንዘብ ወይም መደበኛ ባልሆኑ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ከመጠቀም ይልቅ መደበኛና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን የባንክ ስርዓቶች መጠቀም እንዳለባቸው ይጠበቃል፣

3. የገንዘብ ዝውውራቸውን መከታተልና መነሻና ማዳራሻውን ማረጋገጥ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለይም እርዳታዎች በሚከፋፈሉበት ጊዜ ወይም በሰብአዊ እርዳታ እና በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ በሚሰሩበት ወቅት ለእርዳታ የተዘጋጀው ሀብት ለታሰቡላቸው ተጠቃሚዎች መድረሳቸውን ለማረጋገጥ የገንዘብ መጨረሻ አጠቃቀምን መከታተል እና በሰነድ ማስደገፍ አለባቸው፣

4. አጋሮችን እና ተጠቃሚዎችን ማጣራት፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለተቋቋሙበት ዓላማ የተሰበሰቡ ሀብቶችን በአጋጣሚ ወደ ሽብርተኛ አካላት እንዳይተላለፉ ለመከላከል ከአካባቢው አጋሮች፣ ከንኡሳን ደጋፊዎች ወይም ከአቅራቢዎች ጋር በሚሰሩበት ጊዜ ጥልቅ የፍተሻ እና የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድና ተገቢው ሂደት ውስጥ እንዲያልፍ ማድረግ ይገባል፣

5. የቁጥጥር መመሪያዎችን ማክበርና መተግበር፦ በህግ ተቋቋመው የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተቋቋሙበትን ዓላማ እና ስራዎቻቸው ሳይደናቀፍ ነገር ግን ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ለማስቻል በዓለም አቀፍ ስታንደርድ መሰረት የወጡ የአሰራር ማዕቀፎችን እና የሀገር ውስጥ የቁጥጥር መስፈርቶችን መከተልና መስራት ይጠበቅባቸዋል፣

6. አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ማሳወቅ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወይም ለተቋቋሙለት ዓላማ የተያዘው ለሌላ ዓላማ እንዲውል ወይም አቅጣጫ እንዲቀይር መደረግ ጋር በተያያዘ በቂ ጥርጣሬ ሲኖራቸው ወዲያውኑ ለሚመለከታቸው ባለስልጣናት ለማሳወቅ የሚያስችሉ የውስጥ ቁጥጥር እና የሪፖርት ማድረጊያ መንገዶችን መዘርጋት አለባቸው።

ይህ ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ራሳቸውን ሽብርተኝነትን በገንዘብ መገደፍ ወንጀል ተጠብቀው የተቋቋሙለትን ዓላማ ለማሳካት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል።

ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች  እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ስጋት-ተጋላጭነት ወርክሾፕ---------------------------------------ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች  ሽብርተ...
19/10/2026

ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ ስጋት-ተጋላጭነት ወርክሾፕ
---------------------------------------

ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል ጋር በተያያዘ ያላቸው ስጋት- ተጋላጭነት ጥናት ላይ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ጥናቱ በፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስተባበሪነት በተባበሩት መንግስታት የፀረ-አደንዛዥ ዕፅ ቢሮ ድጋፍ፣ በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን፣ ከፌዴራል የፀጥታና ህግ ማስከበር እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በማሳተፍ የካሄደ ነው።

በጥናቱ ውስጥ ድጋፍ ያደረገው የዴንማርክ ኤምባሲ ተወካይ ሚስ ናታቻ ስኳልደራድ ወርክሾፑን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ የመጠቀም እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን የመዋጋት ተግባር የአንድ ሀገር ብቻ ባለመሆኑ የዴንማርክ መንግስት ወንጀሉን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት የሚያደርጋውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስት የፀረ-አደንዛዥ ዕጽ ቢሮ የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ አብረሃም ልየው በወርክሾፑ ላይ ባደረጉት ንግግር የፀረ-አደንዛዥ ዕጽ ቢሮው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ መጠቀምንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከፌዴራል ፍትህ ተቋማት፣ ከፋይናንስ ዘርፉ እና ከሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልፀው ለትርፍ ካልተቋቋሙ ድርጅቶች ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል ያላቸውን የሪክ ሁኔታ መሰረት ያደረገ እርምጃ በመውሰድ የየራቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ጠቅሰዋል። ከእነዚህ ወንጀሎች መከላከልና መቆጣጠር ጋር በተያያዘ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አከባቢ ስጋት-ተጋላጭነትን መሰረት ያደረግ ስራ ብዙም ያልተለመደ እንደነበር ጠቅሰው በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ መጠቀምና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል መግታት የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ፣ ሚዲያው እና ማህበረሰቡ የየራሱ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ወርክሾፑን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ባለስልጣን መ/ቤቱ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የመመዝገብ፣ የመከታተልና ድጋፍ የማድረግ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ድርጅቶቹ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ ለሰብዓዊ መብት መጠበቅ፣ ለልማት እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት የየራሳቸው ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ባለስልጣን መ/ቤቱ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በተጨማሪም ጥናቱ በጋራ የተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመደገፍ ጋር በተያያዘ ያላቸውን አደጋ በተመለከተ ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት እና ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ከሃብት አጠቃቀም እና ከሽብርተኝነት አደጋ ጋር በተያየዘ በጥናት በተለየው መሰረት ተመጣጣኝ የመካላከል እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በጥናቱ በ2910 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ ዳሰሳ መደረጉን ጠቅሰው ለወንጀሉ ያላቸው ስጋት-ተጋላጭነት (አደጋ) ከፍተኛ የሆኑ ድርጅቶች መለየታቸውን ጠቁመው ወንጀሉን ለመግታት ከድርጅቱ የውስጥ ቁጥጥር የማጠናከር፣ በባንክ ስርዓት የመጠቀምን ሁኔታ ማጠናከር፣ በጥሬ ገንዘብ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት መቀነስ፣ ለስራ የሚያሰማሯቸውን ግለሰቦች ማንነት በአግባቡ ማጣራት፣ ግልፅ የስራ ግንኙነት መፍጠርና ማጠናከር እንዲሁም ጥርጣሬ ሲኖር ለሚመለከታው አካል ማሳወቅ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል። በተጨማሪም ጥናቱ ሲካሄድ ድጋፍ ላደረጉ፣ ላስተባበሩ፣ ለተሳተፉና አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የፋይናንስ ደህንነት ደህንነት አገልግሎት የህግና ዓለም አቀፍ ግዴታዎች ዳይሬክተር ወ/ሮ አቢ ዲንቃ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎትን ወክለው ባስተላለፉት መልዕክት ጥናቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ስታንደርድና መስፈርት መሰረት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎች የስጋት-ተጋላጭነት (አደጋ) ደረጃ በመለየትና በመስራት እንደ ሀገር የሚጠበቅባትን ግዴታ ጭምር መወጣት የሚያስችላት መሆኑን ጠቅሰው ለተግባራዊነቱ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚጠበቅ ጠቅሰዋል።

በመቀጠልም ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀሎች አለም አቀፋዊና ቀጠናዊ ነባራዊ ሁኔታዎች፣ በኢትዮጵያ የሰቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የወንጀሉ ስጋት እና ተጋላጭነት እንዲሁም ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳቶች ላይ የጥናት ውጤቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል። ወርክሾፑ በነገው ዕለትም የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል።

ባንክ ኦፍ አሜሪካ በህግ ጥሰት ከ1.21 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተቀጣ---------------------------------------------የአሜሪካ ትሬዠሪ ዲፓርትመንት (የአሜሪካ ግምጃ ቤት)...
14/10/2026

ባንክ ኦፍ አሜሪካ በህግ ጥሰት ከ1.21 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተቀጣ
---------------------------------------------
የአሜሪካ ትሬዠሪ ዲፓርትመንት (የአሜሪካ ግምጃ ቤት) በአሜሪካ በትልቅነቱ ሁለተኛ በሆነው ባንክ ኦፍ አሜሪካ ላይ ከፍተኛ የህግ እርምጃ መውሰዱ ተገለፀ። ባንኩ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል እና የተጣሉ ማዕቀቦችን ለመተግበር የወጡ ሕጎችን በመጣሱ ምክንያት ከ1.21 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም ይፋ በተደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረት እርምጃው በግምጃ ቤቱ ታሪክ ሦስተኛው ትልቅ የገንዘብ ቅጣት ሲሆን በብሔራዊ የባንክ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት ታሪክ ደግሞ ትልቁ ቅጣት መሆናቸው ተጠቅሷል።

በባንኩ ላይ የተጣሉ ቅጣቶች፣

- የፋይናንስ ወንጀሎች ማስፈጸሚያ መረብ ጋር በተያያዘ፦ ባንኩ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የብሔራዊ ደህንነት ሥጋቶች ለመቀነስ እና ሪፖርት ለማድረግ ባለመቻሉ $1.2 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት እንደተጣለበት ተጠቅሷል።

- በብሔራዊ የባንክ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት፦ የባንኩ የሕግ ማስከበር/በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ ማስመሰል መከላከል ፕሮግራም ጉድለት ያለበት እና ውጤታማ ባለመሆኑ $750 ሚሊዮን ዶላር የአስተዳደራዊ የገንዘብ ቅጣት የተጣለበት መሆኑ ተጠቅሷል።

- የውጭ ሀብቶች ቁጥጥር ቢሮ፦ ባንኩ ከተጠቀሱ አገራት፣ አደንዛዥ ዕፆች እና ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት ላይ የተጣሉትን ጨምሮ በርካታ የማዕቀብ ፕሮግራሞችን በግልጽ በመጣሱ ከባንኩ ጋር የ$11.6 ሚሊዮን ዶላር የስምምነት ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል።

ከተጠቀሱት ዋና ዋና የሕግ ጥሰቶች እና ድክመቶች መካከል፦
ቅጣት የተጣለበት የባንክ ኦፍ አሜሪካ ዋና ዋና የህግ ጥሰት እና ድክመቶች ተብለው የተለዩ የሚከተሉት ናቸው።

- አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሪፖርት አለማድረግ፦ ባንኩ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ አጠራጣሪ የገንዘብ ዝውውሮችን በወቅቱ ሪፖርት ያላደረገ መሆኑን፣

- ውጤታማ ያልሆነ የክትትል ስርዓት፦ ባንኩ ለገቢ ቅድሚያ በመስጠት ለሕግ ማስከበር የሚወጡ ወጪዎችን መቀነሱን እንዲሁም በራሱ አውቶሜትድ ስርዓት አጠራጣሪ ዝውውሮችን ከመለየት ይልቅ በሕግ አስከባሪዎችና በውጭ አካላት ጥቆማ ላይ ብቻ ጥገኛ በመሆኑ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሳይመረመሩ ለረጅም ጊዜ እንዲከማቹ አድርጓል በሚል ተጠያቂ መሆኑ ተጠቅሷል።

- የደንበኞች የጥንቃቄ ፍተሻ መዳከም፦ ባንኩ ደንበኞች ካልታወቁ ሦስተኛ ወገኖች በሚደረጉ ክፍያዎች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ግምት ውስጥ ያላስገባ ሲሆን ከአደንዛዥ ዕፅ እና በንግድ ሽፋን በወንጀል የተገኘ ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ጋር በተያያዘ የታዩ የአደጋ አመላካች ምልክቶችን ችላ ብሏል ሲል ጠቅሷል።

- የማዕቀብ ጥሰቶች፦ ባንኩ በቴክኒክና በሰው ስህተት እንዲሁም ደካማ የማዕቀብ ማንቂያ ስርዓት በመኖሩ ምክንያት ማዕቀብ የተጣለባቸው አገራት እና ዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች በመጣስ 475 የሕግ ጥሰቶችን ፈጽሟል ሲል ተጠቅሷል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የ11.6 ሚሊዮን ዶላር የስምምነት ክፍያ ለመክፈል መስማማቱ ተጠቅሷል።

- አስቀድመው የተላለፉ ትዕዛዞችን አለማክበር፦ የባንኩ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በቂ ሥልጠናና ክህሎት የሌላቸው በመሆናቸው ክፍተቶች እንዲታራሙ ትዕዛዝ ሲሰጥ ያለመተግበር ችግር እንዳለ አመላክቷል።

የተወሰዱ እርምጃዎች እና የማስተካከያ ውሳኔዎች
-----------------------------------
1. የስምምነት ትዕዛዝ፦ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከሦስተኛ ወገን ጋር በመተባበር ያልተለዩ አጠራጣሪ የገንዘብ ዝውውሮችን በመለየት ለሀገሩ የፋይናንስ ደህንነት መ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርግ አስገዳጅ ውሳኔ መተላለፉ ተጠቅሷል።

2. ገለልተኛ የውጭ ግምገማ፦ ባንኩ የክትትል፣ የደንበኞች የጥንቃቄ ፍተሻ እና የባንክ ወኪል ፕሮግራሞቹን ውጤታማነት በተመለከተ ገለልተኛ ግምገማ የማድረግ ግዴታ የተጣለበት መሆኑ ተጠቅሷል።
-------------------------//-------------------

12/10/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩዎች ዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቀዋል።1. ክቡር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)...
08/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩዎች ዛሬው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቀዋል።

1. ክቡር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
2. ክቡር አዲሱ አረጋ - የግብርና ሚኒስትር
3. ⁠ክብርት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር
4. ክቡር መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር
5. ክቡር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
6. ክብርት ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር
7. ክብርት ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
8. ክቡር ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
9. ⁠ክቡር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
10. ⁠ክቡርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ - የጤና ሚኒስትር
11. ክቡር አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
12. ክብርት አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር
13. ክቡር በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
14. ክብርት ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
15. ክብርት ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር
16. ክቡር ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
17. ⁠ክብርት ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
18. ⁠ክቡር ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር
19. ⁠ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
20. ⁠ክቡር መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
21. ⁠ክቡር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
22. ⁠ክቡር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር

08/10/2026

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Financial Intelligence Service-Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Financial Intelligence Service-Ethiopia:

Shortcuts

Share