Ethiopian Embassy Kampala

Ethiopian Embassy Kampala This is the official page of the Embassy of the FDR of Ethiopia in the Republic of Uganda

29/09/2026
29/09/2026

ትልቅ ህዝብ፣ ትልቅ ሀገር፣ ታላቅ ርዕይ

አዲስ አበባ የአፍሪካ ከተሞች ትንሣኤ ምልክት

የነገዋን አፍሪካ ብሩህ ተስፋ በጉልህ እያሳየች የምትገኘው አዲስ አበባ፣ በአሁኑ ወቅት እያስመዘገበች የምትገኘው አንጸባራቂ ለውጥ የአህጉራዊ ከተማ ልማት ፋና ወጊነቷን በግልጽ የሚያረጋግጥ ነው።

ይህ ሽግግር ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ሥልጣኔና ዕድገት አዲስ ተስፋን የፈነጠቀና ትንሣኤን የሚያበስር ተምሳሌት ሆኗል።

የከተማዋ ንፁህ የእግረኛ መንገዶች፣ ዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶች፣ አረንጓዴ ስፍራዎች እና ሰፊ የመንገድ መሰረተ ልማቶች አጠቃላዩ የአፍሪካ የትንሣኤ ሕልም ዕውን ሊሆን እንደሚችል በተግባር ያሳዩ ማረጋገጫዎች ናቸው።

የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫና የአህጉሪቱ የዲፕሎማሲ ማዕከል የመሆኗን ያህል፣ አዲሱ ገጽታዋም የፖለቲካዊ እና የአንድነት መገለጫነቷን ይበልጥ አጉልቶታል።

የከተማዋ ጎዳናዎች በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ስም የተሰየሙ መሆናቸው የአፍሪካን ብዝሃነትና ትስስር የሚያሳይ ሲሆን ይህም አዲስ አበባን የአፍሪካ የጋራ ማንነት እምብርት መሆኗን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች እንደገለጹት፣ ይህ የኮሪደር ልማት የመሠረተ ልማት ግንባታ ብቻ ሳይሆን የቦታ እና የጊዜ ምልከታን በመቀየር የትውልድ ሥነ ልቦና ስብራትን እያረቀ ያለ ታሪካዊ ሥራ ነው።

ይህ ራዕይን ወደ ተግባር የመቀየር ስትራቴጂ በተግባር የተገለጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ማሳያ ሲሆን፣ ለአጭር ጊዜ ሳይሆን ለዘላቂ ትውልድ የሚሻገር አሻራ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ሽግግር ከውበት ባለፈ ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ እና የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን አቅም ያሳደገ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ እያስገኘ ያለ ታላቅ ተግባር ነው።

ቀደም ሲል ለጎርፍ ተጋላጭና የቆሻሻ መጣያ የነበሩ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት ወደ አረንጓዴ፣ ጤናማና ለነዋሪዎች ምቹ ስፍራዎች የተቀየሩ ሲሆን፣ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ ሁለገብ የገበያ ማዕከላትም የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ የበኩላቸውን ሚና እያበረከቱ ነው።

አዲስ አበባ በእግር ለመጓዝ ምቹ፣ አረንጓዴ እና ወጣቶችን ማዕከል ያደረገች የአፍሪካ ከተሞች የለውጥ ምሳሌ መሆኗን በሀገራት መሪዎች፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና በጎብኚዎች ተመስክሮላታል።

የኢዜአ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ፦ https://www.ena.et/web/links

29/09/2026

ምሁራን በሃሳብ የበላይነት የሚያምኑና አዳዲስ ፈጠራዎችን የሚያበረክቱ ሊሆኑ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

29/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድ አቀባበል አደረጉ
*******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መቀበላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

29/09/2026

"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።" Office of the Prime Minister-Ethiopia

28/09/2026
Her Excellency Etsegenet Bezabih Yimenu wishes all Orthodox Christians around the world a happy and peaceful Demera and ...
26/09/2026

Her Excellency Etsegenet Bezabih Yimenu wishes all Orthodox Christians around the world a happy and peaceful Demera and Meskel celebration.
The Ethiopian Meskel celebration is inscribed on UNESCO’s Representative List of the Intangible Cultural Heritage of Humanity, reflecting its profound cultural and spiritual significance.

መልካም የደመራና የመስቀል በዓላት!

The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia Etsegenet Yimenu

25/09/2026

ለሀገር ቤት ቆይታዎ
የሲቢኢ ቱሪስት ካርድ አለልዎ!
******
የሲቢኢ ቱሪስት ካርድ

• በማንኛውም የኤቲኤም እና ፖስ ማሽን የሚገለገሉበት
• ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ የሌለው
• ከሀገር ውጪ ሊጠቀሙበት የሚችሉት

ልክ ሀገርዎ እንደገቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤርፖርት ቅርንጫፍ እና ከተርሚናል ቅርንጫፍ የቱሪስት ካርድን በመውሰድ ቆይታዎን ያሳምሩ!
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

Make Your Stay in Ethiopia Easier with the CBE Tourist Card!
********
CBE Tourist Card gives you a convenient and hassle-free way to make payments during your stay in Ethiopia:

• Use it at ATMs and POS terminals
• No additional service charges
• Can also be used outside Ethiopia

Get your CBE Tourist Card upon arrival at CBE Airport or Terminal Branches and enjoy a more convenient stay in Ethiopia.

CBE Tourist Card — Your convenient companion in Ethiopia!

23/09/2026
23/09/2026

Address

Prince Charles Drive
Kampala

Opening Hours

Monday 09:00 - 16:00
Tuesday 09:00 - 16:00
Wednesday 09:00 - 16:00
Thursday 09:00 - 16:00
Friday 09:00 - 16:00

Telephone

+256414341881

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Embassy Kampala posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share